Mattu University

Yuunivarsiitii Mattuu

መቱ ዩኒቨርሲቲ

Mattu University

Siiqqee women’s Development Assocation News Image
 Uploaded By: Super Admin
 Posted On: Jan 06, 2024

News

መቱ ዩኒቨርሲቲ “Siiqqee women’s Development Assocation” ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚሹ የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች ገቢ የሚሆን የፎቶ ኮፒና ጥረዛ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

(ህውግዳ) ህዳር 25/2016

የመቱ ዩኒቨርሲቲ HIV AIDS መከላከያ ና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ከSWDA ገብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ዓላማውን በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚሹ ሴት ተማሪዎች በኢኮኖሚ ለማገዝ የተቋቋመ የፍቶ ኮፒና ጥረዛ ቤት ነው።

በዚህ የሲቄ ኮፒ ቤት የመክፈቻና የርክክብ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተካልኝ ቀጄላ የሴንቄ ሴቶች ማህበርን በማመስገን ለወደፊቱም ሴት ተማሪዎች በኢኮናሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎል ከመሰል ግበረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በትኩረት አብረን እንሠራለን ብለዋል።

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው HIV AIDS መከላከያ ና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዳይሬክተር መ/ት ትዕግስት ተክሉ በንግግራቸው ይህ መልካም ጅማሮ መሆኑን ጠቅሠው ለወደፊት ከዚህ የበለጠ ለመስራት ማቀዳቸውን እና አንድም ሴት ተማሪ በኢኮኖሚ ችግር ምክኒያት ከት/ት ገበታዋ እንዳትቀር ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የተማሪ ተወካዮች ይህ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎችን ለማገዝ የተቋቋው ኮፒ ቤት ለግቢው ተማሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ድጋፍ የሚሹ ሴት ተማሪዎችም በገቢ የሚደገፍ በመሆኑ የሚበረታታ እና የሚደገፍ ነው በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Gallery

© 2024 Mattu University Disclaimer Privacy Policy